1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጁባ-የደቡብ ሱዳን ሹም ሽርና ሥጋቱ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 19 2008

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ምክትላቸዉን ሪክ ማቸርን ሽረዉ ሌላ መሾማቸዉ ደቡብ ሱዳንን ዳግም ከከፋ ጦርነት ይዶላታል የሚል ሥጋት አሳድሯል። በዘገባዉ መሰረት ሱዳን በወሩ መጀመርያ ላይ ለሦስት ቀናት ዘልቆ ከነበረዉ ጦርነት በኋላ ምክትል ፕሬዚዳንት ሬክ ማቻር የተደበቁበት ቦታ አይታወቅም።

https://p.dw.com/p/1JW2f
Südsudan Präsident Salva Kiir und Vizepräsident Riek Machar
ምስል picture-alliance/dpa/P. Dhil

[No title]

ፕሬዝደንት ኪር ባለፈዉ ነሐሴ በተፈረመዉ የሠላም ሥምምነት መሠረት የተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደትነቱን ሥልጣን የያዙትን የተቃዋሚ መሪ ሪክ ማቸርን ሽረዉ የቀድሞዉን የአማፂ ቡድን ዋና ተደራዳሪ ታባን ዴንግ ጋይን ዛሬ ሾመዋል።

ታባን ዴንግ ጋይ በቅርቡ በተሰየመዉ ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት ዉስጥ የማዕድን ሚንስትር ነበሩ።ኪር ዋናዉን የአማፂ ቡድን መሪ ማቸርን ሽረዉ ታባን ዴንግ ጋይን የሾሙት ማቸር በቅርቡ ጁባ ዉስጥ ከተቀሰቀሰዉ ግጭት በኋላ ተሰዉረዋል በሚል ሰበብ ነዉ።ታባን የቀድሞ አለቃቸዉን ክደዉ ሹመቱን መቀበላቸዉን «በማቸር መሰወር ምክንያት የተፈጠረዉን ክፍተት ለመሙላት ይረዳል በማለት አስታዉቀዋል።ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የቀድሞዉ አማፂ ቡድን የጦር ጄኔራሎችና ሚሊሻዎች አሁንም የማቻር ታማኞች በመሆናቸዉ ሹም-ሽሩ የከፋ ደም መፋሰስ ያስከትላል የሚል ሥጋት አሳድሯል።

ከሦስት ሳምንት ገደማ በፊት በደቡብ ሱዳን ለሦስት ቀናት በዘለቀዉ ጦርነት ወደ 300 ሰዎች ተገድለዋል፤ ከ 37 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ጎረቤት ዩጋንዳ ሸሽተዋል። ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር በሬክ ማቻር ምትክ አዲስ ስለሰየሙት ምክትል ፕሬዚዳንት ናይሮቢ የሚገኘዉን ወኪላችንን በስልክ ጠይነዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ