ጀርመንና ስደተኞች
ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2007ማስታወቂያ
በባልካን ሃገራት አቆራርጠው በሃንጋሪና በኦስትሪያ በኩል ጀርመን የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው ። ስደተኞቹ በብዛት የሚገቡበት የደቡብ ጀርመንዋ ከተማ የሙኒክ ፖሊስ እንዳስታወቀው ዛሬ በየአንድ ሰዓት ልዩነት 100 ያህል ስደተኞች በኦስትሪያ አድርገው ከሃንጋሪ እየገቡ ነው ።ግጭትና በደል ሸሽተው ከሚሰደዱት የአብዛኛዎቹ ምርጫ ከአውሮፓ በህዝብ ብዛትና በኤኮኖሚ እድገት የመጀመሪያውን ስፍራ የምትይዘው ጀርመን ናት ። ጀርመን በብዛት በመግባት ላይ ስላሉት ስደተኞች የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ