1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድህነት መቀነሱ እና ተስፋው

ሐሙስ፣ ጥቅምት 18 2008

ባንኩ በቅርቡ ሊማ-ፔሩ ዉስጥ በተደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ እንዳስታወቀዉ በድሐነት አረንቋ የሚማቅቀዉ ሕዝብ ቁጥር እስካሁን ከነበረዉ ለመጀመሪያ ጊዜ አሽቆልቁላል።

https://p.dw.com/p/1GwCM
Symbolbild Hungernot Afrika
ምስል picture-alliance/dpa

ድህነት መቀነሱና ተስፋው


ከድሐነት ጠገግ በታች የሚኖረዉ የዓለም ሕዝብ ቁጥር መቀነሱን የዓለም ባንክ በቅርቡ ይፋ ባደረገዉ ጥናት አስታዉቋል። ባንኩ በቅርቡ ሊማ-ፔሩ ዉስጥ በተደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ እንዳስታወቀዉ በድሐነት አረንቋ የሚማቅቀዉ ሕዝብ ቁጥር እስካሁን ከነበረዉ ለመጀመሪያ ጊዜ አሽቆልቁላል። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ጥናት ብዙ ጉድለቶች ቢኖሩትም ዉጤቱ ድሕነትን ለመቀነስ ለሚደረገዉ ጥረት ጥሩ ተስፋ ሰጪ ነዉ ተብሏል። በድሕ ሕዝብ ብዛት ቀዳሚዉን ሥፍራ የያዘችዉ አሁንም አፍሪቃ ናት። ገበያዉ ንጉሴ ያጠናቀረዉን ዝግጅት እነሆ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሀመድ