1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳን እና ህጻናት ወታደሮቿ

ሰኞ፣ ነሐሴ 16 2008

ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በአሁኑ ጊዜ ህጻናትን ለውትድርና ከሚመለምሉት ወገኖች መካከል የሱዳን መንግሥትም ይገኝበታል ። መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል ።

https://p.dw.com/p/1JnAq
Südsudan Kindsoldaten
ምስል picture-alliance/dpa/AA/S. Bol

[No title]

የተመ የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ በደቡብ ሱዳን እንደገና ባገረሸው ግጭት ምክንያት ህፃናት ለውትድርና መመልመላቸው እንዳሳሰበው በቅርቡ አስታውቋል ። በጎርጎሮሳዊው 2015 1775 የቀድሞ ህጻናት ወታደሮች በዩኒሴፍ ታዛቢነት ከውትድርና ቢሰናበቱም እንደ አዲስ በተጀመረው ውጊያ ምክንያት ግን ይህ ሁለ መና ሊቀር እንደሚችል አሳስቧል ። ያኔ አብዛኛዎቹ የተለቀቁት የደቡብ ሱዳን ዴሞክራሲያዊ ጦር ከተባለው ቡድን ነበር ። ዩኒሴፍ እንደሚለው በጎርጎሮሳዊው 2016፣ 206 ህጻናት ከተዋጊ ቡድኖች ጋር ተሰልፈው እንዲዋጉ ተመልምለዋል ። ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በአሁኑ ጊዜ ህጻናትን ለewteድርና ከሚመለምሉት ወገኖች መካከል መንግሥትም ይገኝበታል ። መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል ። በዚሁ ጉዳይ ላይ የናይሮቢውን ወኪላችንን በስልክ አነጋግረነዋል።

ፋሲል ግርማ

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ