1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሬዝደንት ኦባማ መልዕክት ፋይዳዉ

Shewaye Legesseእሑድ፣ ሐምሌ 26 2007

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በምስራቅ አፍሪቃና በአፍሪቃ ቀንድ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀዉ ወደመደበኛ ተግባራቸዉ ተመልሰዋል። የእሳቸዉ የኬንያ እና ኢትዮጵያ ጉብኝትም ሆነ በጉብኝታቸዉ ወቅት ያደረጓቸዉ ንግግሮች ግን አሁንም የበርካቶች መነጋገሪያ እንደሆኑ ነዉ። ፕሬዝደንት ኦባማ ገና ለጉብኝት እግራቸዉን ሳያነሱ ሃሳባቸዉን እንዲለዉጡ ከመጠየቅ ጀምሮ፤ የሰብዓዊ መብት ይዞታና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ያሳስበናል ያሉ የመብት ተሟጋቾችም የሁለቱን ሃገራት መሪዎች ሲያገኙ ሊያነሷቸዉ ይገባል ያሏቸዉን ነጥቦች በደብዳቤ ከትበዉ አድርሰዋቸዋል። ፕሬዝደንቱ ባመዛኙ የጉብኝታቸዉ ዋና ዓላማ በሆኑ ጉዳዮች ተጠምደዉ ታይተዋል።

https://p.dw.com/p/1G892