የፕሬዝደንት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት
ሰኞ፣ ሐምሌ 20 2007ማስታወቂያ
ኦባማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም ሀገሪቱ በአፍሪቃ ቀንድ በፀጥታ ረገድ ጉልህ ሚና እንደምትጫወት አመልክተዋል። ፕሬዚደንቱ በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰዉን ፅንፈኛ ቡድን አሸባብን ለመመከት ኢትዮጵያዊውያን ወታደሮች ስላሉ አሜሪካ ሠራዊት ማሠማራት እንደማያስፈልጋትም ገልጸዋል። ጋዜጣዊ መግለጫን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታትሎዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሠ