የጥላቻ ወንጀል በብሪታንያ
ሰኞ፣ ሐምሌ 18 2008ማስታወቂያ
ከምዕራባውያን ሃገራት መካከል በአሁኑ ጊዜ ብሪታንያ ዘረኝነት የከፋባት ሃገር መሆንዋን በቅርቡ ይፋ የተደረገ አንድ ዘገባ አስታውቋል ። እንደ መረጃው በብሪታንያ ከጀርመን አስር እጥፍ የሚበልጥ ከአሜሪካን ደግሞ በአምስት ጊዜ የሚልቅ የፅንፈኝነት ወንጀል ተመዝግቧል ። ብሪታንያ ውስጥ በርዕሰ ከተማዋ በለንደን ፣በሊቨርፑል እና በሌስተር ከተሞች የዘር የሃይማኖት የቀለም ልዩነትን መቀበል በማይፈልጉ ፅንፈኛ ብሪታንያውያን የሚፈፀመው ወንጀል ቁጥር ጨምሯል ። በተለይ የብሪታንያ ህዝብ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት ከወሰነ በኋላ የተባባሰውን ይህንኑ ወንጀል ለመከላከል የብሪታንያ መንግሥት 2.4 ሚሊዮን ፓውንድ መድቧል።
ሃና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ