የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመቀሌ ጉብኝት
ዓርብ፣ ሚያዝያ 5 2010ማስታወቂያ
የትግራይ ህዝብም በሰላም እና ልማት ላይ እንዲያተኩር ጥሪ አቅርበዋል። ከዚያ ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ በሚገኘዉ የሰማዕታት ሃዉልት ሥር ጉንጉን አበባ አኑረዋል። በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልት አዳራሽ የተካሄደውን ውይይት የተከታተሉት በመቀሌ ከተማ የግሎባል የጋዜጠኝነት ኮሌጅ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብረሃ ገብረአረጋዊ እንደነገሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በይበልጥ የኢትዮጵያን አንድነት አጉልተው አንስተዋል።በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የተደመሙት አቶ አብርሃ የተባለው ተግባራዊ ሲሆን ማየት ነዉ የቀረን ሲሉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል አረና ትግራይ የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ማህበረሰቡን ሁሉ ያካተተ አይደለም ሲል ቅሬታዉን ገልፆአል።
አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ