የግሪክ ምክር ቤት በቁጠባ እቅዱ መስማማቱ
ዓርብ፣ ሐምሌ 10 2007ማስታወቂያ
አቴንስ የበፊቱ እዳዋ ወይ እንዲሰረዝላት አለያም የመክፈያ ሁኔታዎች እንዲመቻቹላት ስትወተውት ብትቆይም ያኛዉ እልባት ሳያገኝ ነዉ በድጋሚ ለጠየቀችዉ የ86 ቢሊዮን ዩሮ ብድር በቅድመ ግዴታነት የቁጠባ መርሃግብሮችን ተግባራዊ እንድታደርግ የተስማማችዉ። የግሪክ ምክር ቤት ግን እዚህ ዉሳኔ ላይ ለመድረስ በዉስጡ ከፍተኛ ክፍፍል ተፈጥሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስም ከፍተኛዉ ተቃዉሞ የገጠማቸዉ ከግራዉ የራሳቸዉ ፓርቲ ከሲሪዛ ነዉ። አብዛኞቹ የሲሪዛ አባላት ዉሳኔዉን ግሪክን ያዋረደ ነዉ ሲሉ ተቃዉመዋል። የዚሁ ፓርቲ አባል የሆኑት የግሪክ የአገር ዉስጥ ሚኒስትርም በቅርቡ ማለትም በፊታችን መስከረም አዲስ ምርጫ ሊካሄድ እንደሚችል ጠቁመዋል። ስለግሪክ ምክር ቤት ዉሳኔና በቀጣይ ስለሚጠበቀዉ ርምጃ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለዉ የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሩዋለሁ።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሰ
አርያም ተክሌ