የጋዜጠኛ ኤልያስ የጤና ችግር
ሰኞ፣ የካቲት 20 2009ማስታወቂያ
ላለፉት ሦስት ወራት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የአፍንጫው ጤና መታወኩን እና የተሻለ ህክምና ማግኘት አለመቻሉን ተናገረ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታሰረውን ኤልያስን የሚያሰቃየው የአፍንጫው አለማሽተት ችግር ያጋጠመው ከታሰረ በኋላ መሆኑን ገልጿል። ህክምናውን በጤና ጣብያ እንደሚከታተል የገለፀው ጋዜጠኛ ኤልያስ ከፍ ወዳለ የህክምና መስጫ ሄዶ እንዲታከም እንዳልተጻፈለት የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ