1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማርቲን ሹልዝ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ይሆናሉ

ረቡዕ፣ ጥር 30 2010

የጀርመኗ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል የክርስትያን ዴሞክራቶች ኅብረትና ማርቲን ሹልዝ የሚመሩት የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ ጥምር መንግሥት ለመመስረት ከሚያስችላቸው ስምምነት ደርሰዋል። የጀርመን ሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ ተደራዳሪዎች አድካሚ ቢሆንም በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/2sHtY
Koalitionsverhandlungen Union & SPD | CDU/CSU-Fraktionssitzung
ምስል picture-alliance/dpa/B. Pedersen

በሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ አባላት መፅደቅ ይኖርበታል

አዲስ በሚመሰረተው ጥምር መንግሥት ውስጥ የማርቲን ሹልዝ ፓርቲ በርከት ያሉ የሚኒስቴር ቦታዎችን ያገኛል ተብሏል። ጋዜጦች እንደዘገቡት ማርቲን ሹልዝ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር ይሆናሉ። መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል በያዙት ስልጣን ይቀጥላሉ። የኤኮኖሚ እና መከላከያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በአንጌላ ሜርክል ፓርቲ አመራሮች ይያዛሉ። በስደት ጉዳይ ላይ ጠንከር ያለ አቋም ያላቸው የክርስትያን ዴሞክራቶች ኅብረት አጋር የሆነው የባቫሪያው ክርስቲያን ሶሻል ኅብረት መሪ ሖርስት ሲሆፈር የአገር ውስጥ ጉዳይ ምኒስትር ሆነው ይሾማሉ ተብሏል። ስምምነቱ በ460,000 የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ አባላት መፅደቅ ይኖርበታል።

ይልማ ኃይለሚካኤል 

እሸቴ በቀለ