1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዱር እንስሳ ከፍተኛ ጉባዔ 

ሐሙስ፣ መስከረም 19 2009

የአፍሪቃ ዝሆኖች ጥርስ እና የአዉራሪስ ቀንድ ሽያጭ ዝዉዉር ኢትዮጵያን ጨምሮ የምሥራቅ፤ መካከለኛና የደቡባዊ አፍሪቃ ሃገራትን እያወዛገበ ነዉ። በደቡብ እና ምሥራቅ እስያ ገበያዉ የደራዉ የዝሆን ጥርስ ለሃብት መገለጫ እና ለጥበብ ሥራዎች ይዉላል።

https://p.dw.com/p/2QjnI
Niger Giraffen aus dem Kouré Giraffe Reserve
ምስል Getty Images/AFP/B. Hama

Ber.S.AfrikaIinternational Wildtieren und Schutzkonferenz /MMT - MP3-Stereo

እንዲሁም  የአዉራሪስ ቀንድ ተፈጭቶ በቬትናም እና ቻይና ለባህላዊ መድሐኒትነት በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ ይዉላል። በደቡብ አፍሪቃ በመካሄድ ላይ በሚገኘዉ ዝርያቸዉ ለአደጋ የተጋለጡ የዱር እንስሳትና እጽዋት ዓለም አቀፍ ጉባዔ፤ የዝሆንና መሰል እንስሳት አደን እንዲታገድ፤ አንዳንዶቹም ጠንካራ ቅጣት እንዲጣል በመጠየቅ እየተከራከሩ ነዉ። በዚህ ጉባኤ ላይም ከ2 ሺህ የሚበልጡ ከ180 ሃገራት የተዉጣጡት ተሰብሳቢዎች መገኘታቸዉን የጀርመን የዜና ወኪል DPA አመልክቷል። ደቡብ አፍሪቃ የሚገኘዉ ዘጋቢያችን ዝርዝሩን ልኮልናል። 


መላኩ አየለ


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ