1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ሁኔታ

ሰኞ፣ ሐምሌ 18 2008

ከደቡብ ሱዳን በስተደቡብ ወደ ምትገኘው ኡጋንዳ ባለፈው ሳምንት ብቻ የተሰደዱት ደቡብ ሱዳናውያን ከ24 ሺህ ይበልጣሉ። አብዛኛዎቹም ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ።

https://p.dw.com/p/1JVd4
UNHCR Flüchtlingslage in Gambella Äthiopien
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

[No title]

በደቡብ ሱዳን እንደገና ያገረሸው የርስ በርስ ጦርነት ተጨማሪ ዜጎችን ከሃገራቸው እያሰደደ ነው ።ባለፈው ሳምንት በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 8300 ስደተኞች ኡጋንዳ መግባታቸው ተዘግቧል ። ዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR እንዳስታወቀው ከዚህ ዓመት ጥር ወዲህ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ስደተኛ በአንድ ቀን ኡጋንዳ ሲገባ ያለፈው ሳምንቱ የመጀመሪያው ነው ። ከደቡብ ሱዳን በስተደቡብ ወደ ምትገኘው ኡጋንዳ ባለፈው ሳምንት ብቻ የተሰደዱት ደቡብ ሱዳናውያን ከ24 ሺህ ይበልጣሉ። አብዛኛዎቹም ሴቶች እና ህጻናት ናቸው ። በተመሳሳይ ሁኔታ ደቡብ ሱዳናውያን ወደ ኢትዮጵያም መሰደዳቸው አልቆመም ። በኢትዮጵያ የUNHCR መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ግን ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ቁጥር ከቀድሞው አሁን እየቀነሰ ነው ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ