የዩጋንዳ አጠቃላይ ምርጫ
ሐሙስ፣ የካቲት 10 2008ማስታወቂያ
ሆኖም ዛሬ በዋና ከተማ ካምፓላ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ወረቀቶችና አስፈላጊ ቁሳቁሶች አልቀረቡም ተብሎ ድምጽ መስጠት የሚጀመርበት ጊዜ በሰዓታት መጓተቱ ተሰምቷል። በዚህ ምክንያትም ግጭት መቀስቀሱም ተነግሯል። ዩጋንዳዉያን አስከፊ አገዛዞችን አሳልፈዉ ስልጣን ላይ የወጡት የ71ዓመቱ ዩዌሪ ሙሴቪኒ ለመጪዎቹ ዓመታትም በመንበራቸዉ ላይ ሊሰነብቱ እንደሚችሉ የሚገምቱ ብዙዎች ናቸዉ። አብዛኛዉ ከከተማ ክልል ዉጭ የሚኖር ዜጋ ደጋፊያቸዉ እንደሆነ ይነገራል። ላለፉት ተከታታይ አራት ምርጫዎች እሳቸዉን በመፎካከር ለምርጫ የቀረቡት የቀድሞ ሃኪማቸዉ ኪዛ ቤሲጄ ደጋፊዎች በከተሞች በተለይም ካምፓላ ዉስጥ እንደሚበረክቱ ነዉ ዘገባዎች የሚያሳዩት። የድምፅ ቆጠራዉ ማምሻዉን ይጀምራል ተብሎ ስለሚጠበቀዉ የዩጋንዳ የምርጫ ዉሎ ናይሮቢ ከሚገኘዉ ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ ጋር በአጭሩ ተወያይተናል። ፋሲል ዛሬ ስለነበረዉ የምርጫ ሁኔታ በማብራራት ይጀምራል።
ሸዋዬ ለገሠ
ፋሲል ግርማ
ኂሩት መለሰ