1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የየመን ወቅታዊ ሁኔታ

ሰኞ፣ ጥር 2 2008

ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በየመን የሁቲ አማጽያን ጠንካራ ይዞታ በሆነ አካባቢ የሚገኝ የድንበር የለሽ ሐኪሞች ሆስፒታል በሚሳዔል መመታቱን የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ካስታወቁ በኋላ በየመን የተለያዩ የዉጭ ድርጅቶች መስርያ ቤቶቻቸዉን እየዘጉ መሆኑ ተመልክቶአል።

https://p.dw.com/p/1HbZf
Jemen - Zerstörte Gebäude in Sanaa
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]

ሆስፒታሉን የመታዉ ሚሳይል ከየት እንደተወነጨፈ የታወቀ ነገር ባይኖርም በጥቃቱ ቢያንስ አራት ሰዎች ተገድለዋል ከአስር በላይ ደግሞ መቁሰላቸዉ ታዉቋል። በየመን የሚታየዉ የርስ በርስ ጦርነት በኢራንና በሳዉዲ አረብያ መካከል በቅርቡ የተቀሰቀሰዉ ያለመግባባት ዳግም እንዳያጠናክረዉ እያሰጋም ነዉ። ሳዑዲ ዓረቢያ መራሹ ጥምረት በጎርጎሮሳዊው መስከረም 2014 የሰንዓ ከተማን በተቆጣጠሩት የሑቲ አማጽያን እና አጋሮቻቸው ላይ የአየር ጥቃት መሰንዘር የጀመረው ባለፈዉ መጋቢት ወር መሆኑ ይታወቃል። በሌላ በኩል በየመን የቀጠለዉን የርስ በርስ ጦርነት ለመግታት በሚቀጥሉት ሳምንታት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰላም ድርድር እደሚካሄድ ተሰምቶአል። እዚህ ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በየመን የሚገኘዉን ወኪላችን ግሩም ተክለኃይማኖት በስልክ እንደገለፀልን ሰነዓ ላይ የሚታየዉ ዉጥረት ከትናንት ይልቅ ዛሬ ረገብ ያለ ይመስላል፤ ቢሆንም ሁኔታዉ አሳሳቢ እየሆነ ነዉ።

ግሩም ተክለኃይማኖት

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ