የየመን የለጋሾች ጉባኤ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 19 2009ማስታወቂያ
የርስ በርስ ጦርነት በሚካሄድባት በየመን በገባው ረሀብ ለተጎዱት መርጃ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ ከትናንት በስተያ ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ በተካሄደው የለጋሽ ሀገራት ጉባኤ ላይ ከሚያስፈልገው ገንዘብ ግማሽ ያህል ቃል ተገብቷል ። ጉባኤውን የመሩት የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬስ ድርጅቱ በዚህ ዓመት ለየመን ያስፈልጋል ያለውን ገንዘብ በሙሉ የሚያገኝ ባይሆንም ግማሹንም ቢሆን ለመስጠት ቃል የገቡትን አወድሰዋል ። በአሁኑ ጊዜ በየመን በረሀብ ለተጎዱት ከሚያስፈልገው እርዳታ በተጨማሪ እርዳታውን ለተጎጂዎች እንዴት ማድረስ ይቻላል የሚለውም አሳሳቢ ጉዳይ ነው ።ስለ እርዳታ አሰባሰቡ እና በየመን ለበረሀብ ለተጎዱት እርዳታ ለማድረሱ በሚያጋጥመው ችግር ላይ የብራሰልሱን ወኪላችንን ገበያው ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።