1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዚምባብዌና ሙጋቤ ወቅታዊ ኹኔታ

ዓርብ፣ ኅዳር 8 2010

የዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በሀገሪቱ ጦር የቤት ውስጥ የቁም እስረኛ መደረጋቸው ከተነገረበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ አደባባይ ዛሬ ታይተዋል። ፕሬዚዳንቱ መዲናይቱ ሐራሬ ውስጥ ዛሬ በተከናወነው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ ላይ መገኘታቸው ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/2nqD7

ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በዩኒቨርሲቲ ምረቃ ላይ

የዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በሀገሪቱ ጦር የቤት ውስጥ የቁም እስረኛ መደረጋቸው ከተነገረበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ አደባባይ ዛሬ ታይተዋል። ፕሬዚዳንቱ መዲናይቱ ሐራሬ ውስጥ ዛሬ በተከናወነው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ ላይ መገኘታቸው ተዘግቧል። ቀደም ሲል ሙጋቤን የቁም እስረኛ ካደረጉት የዚምባብዌ ጦር አዛዥ ጄኔራል ኮንስታቲኖ ቺዌንጋ ጋርም እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲሳሳቁም የሚያሳይ የፎቶግራፍ ምስል በተለያዩ የመገናኛ አውታር መንገዶች ተሰራጭቷል። ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በዩኒቨርሲቲ ምረቃው ላይ የተገኙትበትን ምክንያት በማስቀደም ስለዚምባብዌ ወቅታዊ ኹኔታ እንዲኢብራራልን የደቡብ አፍሪቃው ወኪላችን መላኩ አየለን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በስልክ አነጋግሬው ነበር። ከዚምባብዌ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተገናኘ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግሥቴቱ ኃይለ ማሪያምን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የ

መላኩ አየለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ