የዘሄግ የቀይ ሽብር ችሎት የዛሬ ዉሎ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 29 2010ማስታወቂያ
ዘሄይግ በሚገኘዉ የኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት ተፈጽመዋል የተባሉ ዝርዝር በደሎችን ዛሬም የተደመጡ ሲሆን፤ አቃቤ ሕግም በቅጣት ሃሳቡ የዕድሜ ልክ እስራት ጠይቋል። ፍርድ ቤቱ የመቶ አለቃ እሸቱ ዓለሙን ጉዳይ ለፊታችን ሰኞ የቀጠረ ሲሆን የተከሳሹ ጠበቆች መከራከሪያቸዉን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዘሄይግ በሚገኘዉ ፍርድ ቤት የዛሬዉን ችሎት የተከታተሉ እና ኔዘርላንድስ ዉስጥ ከ35 ዓመታት በላይ የኖሩትን አቶ ሲራክ አስፋዉን የተከናወኑን እንዲያስረዱን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ