የኔዘርላንድስ አቃቤ ህግ ማስረጃውን አቅርቧል
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 28 2010ማስታወቂያ
የኔዘርላንድስ አቃቤ ህግ መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ በተባሉት ተከሳሽ ላይ አራት የጦር ወንጀሎች ክስ መስርቷል፡፡ ተከሳሹ በቀይ ሽብር ወቅት በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሀገር የደርግ መንግስት ተቃናቃኞች “እንዲገደሉ፣ እንዲታሰሩ እና እንዲሰቃዩ” አድርገዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ የኔዘርላንድስ አቃቤ ህግ ተከሳሹ “በነሐሴ 1970 ዓ.ም 75 ወጣት እስረኞች እንዲገደሉ ትዕዛዝ መስጠታቸውን እና አስክሬናቸውም በጅምላ እንዲቀበር ማድረጋቸውን” በክሱ ጠቅሷል፡፡
የመቶ አለቃ እሸቱን ጉዳይ እየተመለከተ የሚገኘው የኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት አራት ዳኞች የተሰየሙበት ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ሳምንት ባስቻለው የመጀመሪያ ችሎት የወንጀል ክሱን አስደምጧል፡፡ በሁለተኛው ችሎት ደግሞ ከአሜሪካ፣ ከእንግሊዝ እና ከካናዳ የመጡ ስምንት ምስክሮች ቃላቸው ሰጥተዋል፡፡ የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ በስፍራው በመገኘት ከተከታተለው የኢትዮ ሚዲያ ፎረም ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ አቶ ክንፉ አሰፋ ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ፡፡
ተስፋለም ወልደየስ
ነጋሽ መሐመድ