1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ዜና

ዓርብ፣ ሐምሌ 7 2009

https://p.dw.com/p/2gaDG

ግብጽ ሁርጋዳ በተሰኘ የመዝናኛ ስፋራ ሁለት የዩክሪይን ሴት ሀገር ጎብኝዎች በስለት ተወግተዉ መገደላቸዉን ኧል ማስራ ኧል ዮም  የተባለ አንድ የግብፅ የግል ጋዜጣ መዘገቡ ከተነገረ በኋላ ሌላ በወጣ ዘገባ ሁለቱ ሟቾች የጀርመን ዜጋ መሆናቸዉ ታዉቋል። በጥቃቱ ሁለት የቼክ ሪፓብሊክ ዜጎችን ጨምሮ አራት አገር ጎብኝዎችም መጎዳታቸዉን ታዉቋል። ግድያዉ ለምን እንደተፈፀመ የተገለፀ ነገር የለም።  

 

የጋምቢያ ፕሬዚደንት አዳማ ባሮ መንግሥታቸዉ የቀድሞዉን ፕሬዚደነት ያህያህ ጃሜን ኃብት ለማጣራት አራት ግለሰቦችን ያካተተ አንድ አጣሪ ኮሚሽን ማዋቀሩን ገለፁ።

 

የወቅቱ የአፍሪቃ ኅብረት ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ አዉሮጳ የምታራምደዉ ፖለቲካ ገደብ እንዳያመጣ ሲሉ አስጠነቀቁ። ድንበር በመዝጋቱ የሚያስከተለዉ የሰዎች ሕይወት መቅጠፍ ብቻ ነዉ ሲሉም አዉሮጳን አሳስበዋል።

 

የቻይና መንግሥት የመብት ተሟጋች እና የሠላም ኖቤል ተሸላሚ በቻይናዊዉ ደራሲ፤ በሊዩ ዢያባኦ ሞት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የደረሰበትን ትችትና ወቀሳ አጣጣለ። የቻይና መንግሥት ቻይና ላይ ትችት የሰነዘሩት ሃገራት የቻይናን የሕግ ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ ጠይቀዋል።  

 

የጀርመን ፌዴራል መንግሥት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ጃፓን አሻሽላ ያቀረበችዉን የሞት ቅጣት ብይን ክፉኛ ተቹ። በኢንዱስትሪ ከበለፀጉት ሃገራት መካከል ጃፓን እንደ ዩናይትድ ስቴትስ የሞት ቅጣት መፈጸሟን የቀጠለች ሀገር ናት።