1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ዜና

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 4 2009

https://p.dw.com/p/2gMSS

የምሽቱ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 

በሶማሌላንድ ባለሥልጣናት የተያዘዉ የቴሌቬዥን ጋዜጠኛ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቅ ለጋዜጠኞች መብት የመቆረቆረዉ ድርጅት «CPJ» አሳሰበ። ጋዜጠኛዉ የታሰረበት ቦታ እንደማያዉቁ ቤተሰቦቹ እየገለፁ ነዉ።

ዩኤስ አሜሪካ እና ኳታር ሽብርተንነትን ለመዋጋት የመግባብያ ሰነድ መፈራረማቸዉ ተገለፀ። ነገ ርያድ ላይ አራቱ የአረብ ሃገራትና ዩኤስ አሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ይሰበሰባሉ።

 

በቱርክ የከሸፈዉ የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ አንደኛ ዓመት በመላዉ ሃገሪቱ ዛሬ መታሰብ መጀመሩ ተመለከተ። ዝግጅቱ ለአንድ ሳምንት እንደሚቀጥል ታዉቋል።

 

የቡድን 20 ጉባዔን ባስተናገደችዉ በጀርመንዋ ሐምቡርግ ከተማ የታየዉን የተቃዋሚዎች ከፍተኛ ኃይል የቀላቀለ ረብሻ ተከትሎ ብጥብጡን ያካሄዱትን ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ለማድረግ የጀርመን ፊደራል መንግሥት የአዉሮጳ አባል ሃገራትን ለትብብር መጠየቁ ተሰማ።  ከሌሎች የአዉሮጳ ሃገራት የመጡ በርካታ ጋጠወጥ ረብሸኞች ሰላማዊ ተቃዉሞዉን መረበሻቸዉ ተመልክቷል።