1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ዜና

ሰኞ፣ የካቲት 13 2009

https://p.dw.com/p/2XwGH

ዓለም እንዴት ዋለች! የምሽቱን የዓለም ዋና ዋና ዜና ከዶይቼ ቬለ ተከታተሉ!

የደቡብ ሱዳን መንግሥት በአገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች ውስጥ ረሃብ መኖሩን በይፋ አስታወቀ። በሃገሪቱ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ሌሎች ነዋሪዎች ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸዉን  ሦስት ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት የጋራ መግለጫ  አሳስበዋል።

 

የዩኤስ አሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ሃገራቸዉ ከአዉሮጳ ኅብረት ጋር በቅርበት መሥራት እንደምትፈልግ አስታወቁ። ይህን ዜና የአውሮጳ ኅብረት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ቱስክ « ሰናይ መልዕክት» ሲሉ ገልፀዉታል።

 

የጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ወደ ሰሜናዊትዋ አፍሪቃዊት  ሃገር ወደ አልጀርያ ለመጓዝ የያዙት እቅድ ፕሬዚዳንቱ በመታመቻቸዉ በመጨረሻ ሰዓት መሰረዛቸዉ  ተመለከተ። በአፍሪቃ ትልቅ የቆዳ ስፋት ያላት አልጀርያ ከማሊና ከኒጀር ወደ አዉሮጳ ለሚፈልሱ ስደተኞች መሸጋገርያ ሃገር መሆንዋ ይታወቃል።

የምሽቱን የዓለም ዜና ያድምጡ!