1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና

Lidet Abebeቅዳሜ፣ ሚያዝያ 19 2016

የሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና

https://p.dw.com/p/4f1vL

  

የሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም  አርዕስተ ዜና

በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ የተሳፈሩበት የእንጨት ጀልባ በመስመጧ ወንዝ ውስጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 58 ደረሰ። የጀልባዋ መስመጥ መንስኤ ከአቅም በላይ ሰዎችን ማሳፈሯ ነበር።

 

እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በምትገኘው ራፋህ ከተማ ሌሊቱን በሰነዘረችው ጥቃት  18 ሰዎች ተገደሉ ። በጥቃቱ ከሞቱት መካከል 14ቱ ህጻናት መሆናቸውን የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

 

ዩክሬንን ለመርዳት ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተስማማበትን የርዳታ ጥቅል የውሳኔ ረቂቅ የጀርመን መንግሥት አወደሰ።

 

ዛሬ በተካሄደው 41ኛው የቪየና ከተማ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው ጫላ ረጋሳ አንደኛ በመሆን አሸነፈ። በ 44ኛው የለንደን ማራቶን ውድድርም ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች በወንዶች ቀነኒሳ በቀለ ፤ በሴቶች ደግሞ ትዕግስት አሰፋ ተጠባቂውን ውድድር ሁለተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ከዚሕ ዝግጅት ተጨማሪ

ከዚሕ ዝግጅት ተጨማሪ

Äthiopien Alamata City Gondar
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-News-DWcom

የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።