1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ዜና

Mantegaftot Sileshi Siyoumቅዳሜ፣ ግንቦት 13 2008

ከፓሪስ ወደ ካይሮ ሲበር እየተመዝገዘገ የሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ የተከሰከሰው የግብጽ አውሮፕላን የአብራሪ ክፍል ውስጥ ጭስ ተከስቶ እንደነበር የፈረንሳይ የበረራ አደጋ ባለሙያዎች ዛሬ አስታወቁ። ለዓመት የዘለቀውን የቡሩንዲ ቀውስ ለመፍታት ያለመው የሠላም ንግግር ታንዛኒያ አሩሻ ከተማ ውስጥ ዛሬ በድጋሚ ተጀመረ። ከሁለት ዓመት በፊት ዩክሬን ውስጥ በሚሳይል ተመትቶ የወደቀው የማሌዢያ MH17 አውሮፕላን አደጋ ሰለባ ቤተሰቦች በጉዳት ካሣ ጉዳይ ሩስያን እና ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ከሰሱ። አውሮፕላኑ የተመታው በሩስያ ሠራሽ ሚሳይል ነበር።

https://p.dw.com/p/1IsON