1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ዜና

Azeb Tadesse ሐሙስ፣ ጥር 11 2009

https://p.dw.com/p/2W56k

የምሽቱ አርስተ ዜና

በጋምቢያ የተቀሰቀሰዉ ፖለቲካዊ ቀዉስ እንደቀጠለ ነዉ። የሀገሪቱ ጦር ሠራዊት አዛዥ በዚህ የፖለቲካ ዉዝግብ ዉስጥ እሳቸዉም ሆነ ሠራዊታቸዉ እንደማይገባ አስታዉቀዋል።

በኢራን ዋና መዲና ቴህራን አንድ ፎቅ ቤት ላይ የተነሳን እሳት ለማጥፋት የተሰማሩ 30 የእሳት አደጋ ሠራተኞች በአደጋዉ ሞቱ።

ተሰናባቹ የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ትናንት ምሽት በሰጡት የመጨረሻ ጋዜጣዊ መግለጫ ነገ በይፋ ስልጣናቸዉን ለሚረከቡት ለተመራጩ የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ማሳሰብያ አስተላለፉ።