የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤትና አፍሪቃ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 16 2009ማስታወቂያ
የዓለም አቀፉን የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ሥራ-እና ዓላማ የሚቃወሙ የአፍሪቃ ሐገራት ከፍርድ ቤቱ አባልነት እየወጡ ነዉ።እስካሁን ቡሩንዲ፤ ደቡብ አፍሪቃ እና ጋምቢያ የመሰናበቻ ደብዳቤያቸዉን አስገብተዋል። ሌሎቹ ሃገራትም እነሱን ተከትለዉ ለመዉጣት ዳርዳር ማለታቸዉ ተሰምቷል። በብዙዎቹ የአፍሪቃ መንግሥታት ዘንድ ይህ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ተቀባይነት እያጣ መጥቷል። የዶቼ ቬለዉ አቡበከር ያሎ እንደሚለዉ ፍርድ ቤቱ የበለጠ ተቀባይነት እንዲኖረዉ ወደ ፊት ለዉጥ አድርጎ በአዲስ የአሰራር ዘዴ መዋቀር ይኖርበታል። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ሐተታዉን እንደሚከተለዉ አዘጋጅቶታል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሸዋዬ ለገሰ