የዓለም ንግድ ድርጅት ሥራ እና አሠራር
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 18 2010ማስታወቂያ
የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) ዓላማ እና አሠራር ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ወገኖችን እንዳከራከረ ነዉ። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ለድሆች የሚቆረቆሩ ተቋማት እና የምጣኔ ሐብት አዋቂዎች ዓለም አቀፉ ድርጅት የመሥራቾቹን የምዕራባዉያንን ፍላጎት እና ጥቅም ለማስከበር የቆመ ነዉ ይላሉ። የምዕራቡን ዓለም የምጣኔ ሐብት መርሕ የሚያቀነቅኑ ባንፃሩ ዓለም አቀፉ የንግድ ድርጅት ለድሆችም፤ ለበለፀጉትም ሐገራት ሕዝብ እኩል ጠቃሚ ነዉ ባይ ናቸዉ። የዛሬዉ ከኤኮኖሚዉ ዓለም ዝግጅታችን ክርክሩን ባጭሩ ይቃኛል። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ነዉ ያዘጋጀዉ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ