1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዋሽንግተን ሃቫና አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ

ሰኞ፣ ሐምሌ 13 2007

ከጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመድ ከ1961ዓ,ም ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘዉ የኩባ ኤምባሲ ዛሬ የኩባ ሰንደቅ ዓላማ ተዉለብልቧል። በዩናይትድ ስቴትስና ኩባ መካከል ለ54ዓመታት ተቋርጦ የከረመዉ የዲፕሎማሲ ትስስር በአዲስ ምዕራፍ የታደሰበት ምልክት።

https://p.dw.com/p/1G1jv
Symbolbild Kuba USA Flaggen
ምስል picture alliance/Photoshot

[No title]

አሁን በሃቫናም እንዲሁ በአሜሪካን ኤምባሲም እንደዋሽንግተኑ የኩባ ኤምባሲ በይፋ ተከፍቷል። የኩባ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡሩኖ ሮድሪገዝ ዋሽንግተን ብቅ ብለዉ ከአሜሪካዉ አቻቸዉ ጆን ኬሪ ጋ ይነጋገራሉ የሀገራቸዉ ሰንደቅ ዓላማም በአዲሱ የዲፕሎማሲ ግንኙነት መሠረት በኤምባሲያቸዉ ላይ ሲዉለበለብ ያስተዉላሉ። ኬሪም በቀጣዩ ወር ወደሃቫና ይጓዛሉ። ኩባና አሜሪካ ለረዥም ጊዜ ተቋርጦ የቆየ ግንኙነታቸዉን ለማደስ እጅግም ሳይሰማ ዉስጥዉስጡን ሲያካሂዱት የቆዩት ድርድር ከዳር መድረሱ ከተሰማ ሰባት ወራት ተቆጥረዋል። ዉይይት ድርድሩ ልዩነቶቻቸዉን ፈትቶ ጨርሷል ባይባልም ዛሬ ደግሞ በይፋ አንዳቸዉ በሌላቸዉ ዋና ከተማ የሚገኝ ኤምባሲያቸዉን በመክፈት ግንኙነታቸዉን አድሰዉ ታይተዋል። የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ የኩባና ዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማሲያዊ ትስስር በይፋ ስልተጀመረበት ሁኔታ በስልክ አነጋግሬዋለሁ። ዛሬ ዋሽንግተን በሚገኘዉ የኩባ ኤምባሲ ስለተከናወነዉ መክብብ እንዲህ ገልጾልኛል፤

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ