1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የዉጭ ዜጎችን ያስደነገጠዉ ሕግ በሳዉዲ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 20 2009

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ከሹፌርና ከቤት ሠራተኞች በስተቀር በግዛቱ የሚኖሩ የውጭ ሀገር   ዜጎችም ሆነ ሚስትና ልጆቻቸው ወርኃዊ ክፍያ እንዲከፍሉ ሊያደርግ ነው፡፡

https://p.dw.com/p/2V1Hf
Banknoten aus Saudi Arabien Geld Gelscheine
ምስል picture-alliance/dpa/T. Brakemeier

MMT-Beri. Riyadh (saudi new taxation) - MP3-Stereo

የዓመቱ የበጀት ማጽደቂያ ጉባዔ ላይ በሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስትር ይፋ የተደረገው መርሐ ዕቅድ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት እየጨመረ የሚሄድ የክፍያ ስርዓት ከመጪው የፈረንጆች አመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ አመልክቷል፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ሐምሌ እንደሚጀምር የተገለጸው የቤተሰብ ወርሐዊ ክፍያ በልጅ ከአንድ መቶ የሳዑዲ ሪያል ጀምሮ ሦስተኛው ዓመት ላይ በወር ለአንድ ልጅ 400 የሳዑዲ ሪያል ይደርሳል፡፡ እቅዱ በሳዑዲ የሚሰሩ የውጭ ሐገር ዜጎችን አስደንግጧል ፡፡ ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ