1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወጣቶች ዓሣ እርባታ በጋና 

Merga Yonas Bula
ዓርብ፣ ሰኔ 15 2010

በጀርመንዋ ቦን ከተማ ባለፈዉ ሳምንት «Global Media Forum» ማለትም «ዓለም ዓቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ» የተሰኘ የመወያያ መድረክ ለሦስት ቀናት ተዘጋጅቶአል። የዉይይቱ ዋና ነጥብ «የዓለምአቀፍ ኃብት ክፍፍል ኢፍትሃዊነት» የሚል ነበረ።

https://p.dw.com/p/302tS
DW Sendung Eco@africa Fischer in Ghana
ምስል DW

የጋና ወጣቶች የዓሣ እርባታ

በጀርመንዋ ቦን ከተማ ባለፈዉ ሳምንት «Global Media Forum» ማለትም «ዓለም ዓቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ» የተሰኘ የመወያያ መድረክ ለሦስት ቀናት ተዘጋጅቶአል። የዉይይቱ  ዋና ነጥብ የነበረዉ  «የዓለምአቀፍ ኃብት ክፍፍል ኢፍትሃዊነት» የሚል ነበረ። በጋና የነዳጅና የጋዝ እምቅ ኃብት በሃገሪቱ ያለዉን የድኅነት ሁኔታ ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል። ግን እነዚህ ኢንዱስትሪዎች የሠራተኛ ኃይል ከዉጭ መቅጠራቸዉ በርካታ የጋና ወጣቶችን ሥራ አጥ አድርጎአል። አዲሱ የዓሣ አረባብ ፖሊሲ ብዙ ሰዎችን ቢያበሳጭም በጋና ምዕራባዊ ክፍል «የኑሮ መሠረት ማስፋፋት መረሃ-ግብር» በሚል ርዕስ ወጣቶች እንዴት «Catfish» የተሰኘዉ ዓሣ ማርባት እንደሚችሉ ስልጠና ተሰቷቸዋል። በዚህ መረሃ-ግብር የኃብት ክፍፍል ኢፍትሃዊነት ይቀንሳል ተብሎም ተስፋ ተደርጎበታል። በአሁኑ ወቅት ቁጥሩ እየበዛ የመጣዉ ወጣት ተስፋዉ እየጨመረ ያለዉ ካት-ፊሽን በማርባት ላይ ሆኗል።   
መርጋ ዮናስ / መክስ ሱክ
አዜብ ታደሰ