1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ፕሬዚደንታዊ እጩዎች እና የአስመራጩ ኮሚሽን ውይይት

ረቡዕ፣ መስከረም 24 2010

የኬንያ አስመራጭ ኮሚሽን በቀጣዩ ጥቅምት ወር መጨረሻ ገደማ ድጋሚ ይካሄዳል በሚባለው ፕሬዚደንታዊ  ምርጫ ላይ የተደቀኑ እክሎችን ለማስወገድ ይቻል ዘንድ በምርጫው ከሚወዳደሩት ተቀናቃኞቹ ፓርቲዎች ጋር በትናንቱ ዕለት በተናጠል ውይይት አካሄደ።

https://p.dw.com/p/2lDhu
Kenia Skyline Nairobi
ምስል picture-alliance/World Pictures/Photoshot/P. Phipp

ኬንያ

በምክትል ፕሬዚደንት ዊልያም ሩቶ እና በራይላ ኦዲንጋ የተወከሉት የገዢው ጁብሊ ፓርቲ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት፣ በምህጻሩ ናሳ ከውይይቱ በኋላ በየበኩላቸው ጋዜጣዊ መግለጫ  ሰጥተዋል። በመግለጫዎቹ ሁለቱ ወገኖች ሰፊ የሀሳብ ልዩነት እንዳላቸው ጎልቶዋል። ስለአስመራጩ ኮሚሽን እና ስለፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ውይይት ናይሮቢ የሚገኙትን አቶ ፍቅረማርያም መኮንን በስልክ አነጋግሬአቸዋለሁ።

አርያም ክሌ

ነጋሽ መሀመድ