1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ዉሳኔ አንድምታዉ

ሰኞ፣ ጥቅምት 28 2009

ኬንያ ከተመድ ጋር በገባችበት ዉዝግብ ምክንያት የደቡብ ሱዳን ሰላማዊ ዜጎች ሰብዓዊ ይዞታ ለአደጋ መጋለጥ እንደማይኖርበት የሚያሳስቡ ዘገባዎች እየወጡ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2SIGU
Somalia Kenianische Soldaten im Kampf gegen gegen Al-Shabaab
ምስል picture alliance/AP Photo/B. Curtis

Q&A Kenya controversy - MP3-Stereo

 

ናይሮቢ ደቡብ ሱዳን የሚገኙ ሰላም አስከባሪዎች ሲቪሉን ዜጋ ለጥቃት መከላከል አልቻሉም በሚል ከመንግሥታቱ ድርጅት በቀረበ ትችት እና እዚያ የሚገኙ የሰላም አስከባሪዉ ኃይል የበላይ የሆኑ ዜጋዋ ከቦታዉ መነሳታቸዉን አልተቀበለችም። ሰላም አስከባሪ ሠራዊቷን ከደቡብ ሱዳን እንደምታስወጣ እና በመንግሥታቱ ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮም እንደማትሳተፍ አስታዉቃለች። የኬንያ ርምጃ ሊያስከትል የሚችለዉን ከወዲሁ በመመዘን ተግባራዊ ማድረግ እንደሌለባት የሚመክሩ እንዳሉ ሁሉ፤ የተመድ ክስ በአካባቢዉ የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴ የናይሮቢን ሚና ከግምት አላስገባም የሚሉም አሉ። ከናይሮቢ ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም መኮንንን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በጉዳዩ ላይ አነጋግረነዋል።

ፍቅረማርያም መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ