1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦክስፋም ቅሌት እና የአውሮፓ ህብረት ማስጠንቀቂያ

ሐሙስ፣ የካቲት 15 2010

መቀመጫውን በብሪታንያ መዲና ለንደን ያደረገው የኦክስፋም ተራድኦ ድርጅት ለእርዳታ ስራ በተሰማሩባቸው አካባቢዎች የጾታ ጥቃት አድርሰዋል፣ በገንዘብ ደልለው ወሲብ ፈጽመዋል የሚል ወቀሳ ከተሰማ ወዲህ የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ስነ ምግባር እና ተጠያቂነት ጉዳይ የሰሞኑ ዋና መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡

https://p.dw.com/p/2tAK9
Uk Oxfam-Sex-Skandal | Logo
ምስል Getty Images/AFP/A. Buchanan

የኦክስፋም ቅሌት እና የአውሮፓ ህብረት ማስጠንቀቂያ

መቀመጫውን በብሪታንያ መዲና ለንደን ያደረገው የኦክስፋም ተራድኦ ድርጅት ለእርዳታ ስራ በተሰማሩባቸው አካባቢዎች የጾታ ጥቃት አድርሰዋል፣ በገንዘብ ደልለው ወሲብ ፈጽመዋል የሚል ወቀሳ ከተሰማ ወዲህ የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ስነ ምግባር እና ተጠያቂነት ጉዳይ የሰሞኑ ዋና መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡ የኦክስፋም ሰራተኞች አደረሱት የተባለውን የጾታ ጥቃት እና የድርጅቱን ቸልተኝነት ያጋለጠው ዘ ታይምስ የተባለው ጋዜጣ የብሪታንያ ጋዜጣ ነው፡፡ የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ለኦክስፋም ከፍተኛ ድጋፍ ከሚያደርጉት ውስጥ አንዱ የሆነው የአውሮጳ ህብረት ለተራድኦ ድርጅቱ ቅሌት የሰጠውን ምላሽ አካትቶ ዘገባ አጠናቅሯል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ