የኦሮሞ የሕግ ሙያተኞች ማኅበር
ሰኞ፣ ጥቅምት 14 2009ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ የኦሮሞ ተቃውሞን መነሻ ያደረገ የኦሮሞ ተወላጆች የሕግ ባለሞያዎች ማኅበር ያዘጋጀው ጉባኤ ተካሂዷል። የጉባኤው አዘጋጆች እና ተሳታፊዎች ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት ጉባኤው በኦሮሞ ተቃውሞ እና ባስገኘው ውጤት ላይ ተነጋግሯል። እንደ ተሳታፊዎቹ የጉባኤው ዓላማ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን የሚያስማማ አንድ አግባቢ ሃሳብ ላይ መድረስ እንጂ ከጉባኤው በፊት እንደተወራው የኦሮምያን የመተዳደሪያ ደንብ ማውጣት ወይም የኦሮምያን ጦር ማቋቋም አልነበረም። የለንደኑ ዘጋቢያችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ድልነሳ ጌታነህ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ