የኦሮሚያ ግጭትና ኦፌኮ
ዓርብ፣ የካቲት 11 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሚያ መስተዳድር የቀጠለዉን ግጭት ለማስቆም ጉዳዩ የሚመለከታቸዉን ወገኖች ሁሉ እንዲያነጋግር የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ፕሬዝደንት ጠየቁ።የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ ባጭሩ) ዋና ፀሐፊና የኦፌኮ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ገብሩ ገብረ ማርያም እንደሚሉት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተቀጣጠለዉ ተቃዉሞና አመፅ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም እየተዛመተ ነዉ።መግሥት አመፁን በሐይል ለመደፍለቅ ከመሞከር ይልቅ ሕዝቡ ከሚያምንባቸዉ የሐገር ሽማግሌዎች፤ ከጎሳ መሪዎች እና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በመነጋገር መፍትሔ መፈለግ አለበት።አቶ ገብሩን በስልክ አነጋግሬቸዋለሁ።
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ