የእነ ጋዜጠኛ ኤልያስ የፍርድ ሂደት
ማክሰኞ፣ ግንቦት 29 2009ማስታወቂያ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሚት ምድብ ችሎት በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና ፖለቲከኛ ዳንኤል ሽበሺ ጉዳይ ላይ አቃቤ ህግ የሰጠውን መልስ እና የተከሳሽ ጠበቃን መቃወሚያ መርምሮ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ችሎቱ በዛሬው ውሎው አቃቤ ህግ የተከሳሽ ጠበቃ ላቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሰጠውን ምላሽ አዳምጧል። ኤልያስ እና ዳንኤል ከ6 ወራት እስር በኋላ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ነበር ፍርድ ቤት የቀረቡት። የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ የተከታተለው የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ