የእነ አቶ በቀለ ገርባ የፍርድ ቤት ውሎ
ረቡዕ፣ ግንቦት 30 2009ማስታወቂያ
ከተከሳሾቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ አዲሱ ቡላላ ለፍርድ ቤቱ "መጉላላቱ አግባብነት የለውም። ከእናንተ ጀርባ የደኅንነት እጅ እንዳለ ይገባናል። እያከናወናችሁት ባሉት ተግባራት እናንተንም አገራችንንም እንድንጠላ እያደረጋችሁን ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን(ኢቢሲ) ተተርጉሞ በሚቀርበው ሰነድ ላይ ተመርኩዞ ብይን ለመስጠት ለዛሬ የሰጠውን ቀጠሮ እንደገና ለአምስተኛ ጊዜ አራዝሞታል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
እሸቴ በቀለ