የእስራኤል የመንግሥታቱ ድርጅት ዉሳኔ ተቃዉሞ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 18 2009ማስታወቂያ
እስራኤል ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ውሳኔ በኋላ ከ12 ሃገራት ጋር ያላትን የሥራ ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቃለች። እስራኤል ከሃገራቱ ጋር የሥራ ግንኙነቱን ያቋረጠችው በምዕራብ ዮርዳኖስ እና ምሥራቅ ኢየሩሳሌም የአይሁድ ሰፈራን በማውገዝ የመንግሥታቱ ድርጅት ዐርብ እለት ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም ነው። ስቱዲዮ ከመግባቴ ቀደም ብሎ የእየሩሳሌም ወኪላችን ዜናነህ መኮንንን በስልክ አነጋግሬው ነበር። ዜናነህ ውሳኔው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንሥትር የዓመታት ውዝግብ ውጤት ነዉ ብሏል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ/ ዜናነህ መኮንን
አዜብ ታደሰ