1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን የገና በዓል አከባበር በጀርመን

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 15 2008

ለትምህርትም ሆነ ለሥራ ወደ ጀርመን መጥተው ሲኖሩ የሀገር ቤት ናፍቆቱ እንዲህ በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም። ቤተሰብን፣ አየሩን እና ምግቡን መናፈቅ እንዲሁም ስነልቦና ላይ የሚኖረው ተፅዕኖም ጎልቶ የሚታየዉ በደስታ ወይም በሐዘን ጊዜ ነው።

https://p.dw.com/p/1HTq3
Berlin Brandenburger Tor Weihnachtsbaum
ምስል Reuters/F. Bensch

[No title]

የበዓል ናፍቆቱን ለማሟላት ብዙ ነገሮች ይደረጋሉ። ዓመት በአሎች ሲመጡ የሀገር ቤት ናፍቆቱ ወይም ጀርመኖቹ እንደሚሉት (heimweh) ለየት ያለ መልክ ይይዛል። ኢትዮጵያ በምትከተለው የቀን ቀመር መሠረት ገናን ለማክበር ገና አንድ ሳምንት ይቀራል። ለትምህርት ወደ ጀርምን ሀገር የመጡ ተማሪዎች እንዴት የጀርመንን ገና እንደሚያሳልፉ፣ የአገርቤት ናፍቆቱንስ እንዴት እንደሚቋቋሙ ይናገራሉ።

መርጋ ዮናስ

ማንተጋፍቶት ስለሺ