1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃዋሚዎች የኢትዮጵያ መንግስትን ተችተዋል

ረቡዕ፣ ጥር 30 2010

በብሪታኒያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የወሰዱትን እርምጃ በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በእስር ላይ የሚገኙት "አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እና ጋዜጠኞች ይፈቱ" የሚል መፈክር ማሰማታቸውን የተቃውሞ ሰልፉን የታዘበው የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ድልነሳ ጌታነሕ ተናግሯል።

https://p.dw.com/p/2sHqr
Äthiopier protestieren in London
ምስል DW/D. Getaneh

የመንግስትን እርምጃ ያወገዘው ተቃውሞ

በብሪታኒያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የወሰዱትን እርምጃ በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። የተቃውሞ ሰልፉ ተሳታፊዎች የብሪታኒያ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲያሳድር ጠይቀዋል። በእስር ላይ የሚገኙት "አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እና ጋዜጠኞች ይፈቱ" የሚል መፈክር ማሰማታቸውን የተቃውሞ ሰልፉን የታዘበው የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ድልነሳ ጌታነሕ ተናግሯል። ትራፍ ላጋር በተባለው የለንደን ከተማ አደባባይ የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፉ ወደ አገሪቱ ከጠቅላይ ምኒስትር ቴሬሳ ሜይ ቢሮ ደጃፍ አምርቷል። ድልነሳ ጌታነህን በስልክ የሰልፉን አዘጋጆች በማነጋገር ማብራሪያ ሰጥቷል።

ሙሉ ዘገባውን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ

ድልነሳ ጌታነህ

እሸቴ በቀለ