1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን ስደትና መፍትሄው

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 20 2007

በየመን በደቡብ አፍሪቃ እና በሌሎችም የአፍሪቃ ሃገራት መውጫ አጥተው የሚሰቃዩ ና ለተለያዩ ጥቃቶች የተዳረጉትም ቁጥር ቀላል አይደለም ።

https://p.dw.com/p/1FEfi
Libyen Migranten im Abu Salim Zentrum
ምስል picture-alliance/dpa

በተለያዩ ሃገራት በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚያጋጥሟቸው ችግሮችና መከራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ በመሄድ ላይ ናቸው ። የፀጥታ ችግሮች ባሉባቸው አንዳንድ የአረብ ሃገራት ኢትዮጵያውያዊ በአሁኑ ጊዜ በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ ና እየተሠቃዩ ነው ። ሰሞኑን ሊቢያ ውስጥ እስላማዊ መንግሥት እያለ ራሱን በሚጠራው ቡድን ዘግናኝ ግድያ የተፈጸመባቸው 30 ኢትዮጵያውያን በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ናቸው ። ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ አንድ ኢትዮጵያዊ ሆን ተብሎ በተለኮሰ እሳት መገደሉ ሌላ ደግሞ ለከባድ ጉዳት መዳረጉ አሳዝኖ ሳያበቃ የተከለው ይህ አሰቃቂ ግድያ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያስቆጣና ያሳዘነ ዐብይ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል ። በሜዲቴራንያን ባህር በኩል በአደገኛ የባህር ላይ ጉዞ ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ ህይወታቸው የሚያልፍ ኢትዮጵያውያንም ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም ።በአሁኑ ጊዜ ውጊያ በሚካሄድባት በየመን የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያንም ቁም ስቅል ላይ ናቸው። እነዚህን የመሳሰሉ መከራዎች የሚደርሱባቸውን ዜጎች ለመርዳት የኢትዮጵያ መንግሥት የበኩሉን ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ቢያሳውቅም የስደተኞቹን ችግር አለማቃለሉ ነው የሚነገረው ። ኢትዮጵያውያን ለ ሞት እና ለቁም ስቅል የሚዳርገው የዚህን መሰሉ ስደት መንስኤ ምንድነው ? መፍትሄውስ ? የዛሬው እንወያይ ዝግጅት ርዕስ ነው ። በዚህ ርዕስ ላይ እንዲወያዩልን አራት እንግዶችን ጋብዘናል ። እነርሱም ። አቶ እውነቱ ብላታ ደበላ የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ዴታ ፣አቶ ቁምላቸው ዳኜ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በምህፃሩ ኢሰመጉ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ታገል ሰሎሞን የዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት በምህፃሩ IOM ባልደረባ እንዲሁን የዶቼቬለ የአማርኛ ክፍል የብራሰልስ ዘጋቢ ገበያው ንጉሴ ናቸው ።ውይይቱን ከድምፅ ማዕቀፉ ይከታተሉ

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ