1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያና ኬንያን የሚያገናኘዉ አዉራ ጎዳና ሥራዉን ሊጀምር ነዉ 

ሐሙስ፣ ኅዳር 15 2009

ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያገናኘዉና 500 ኪሎሜትር ርዝመት ያለዉ አዉራ ጎዳና ግንባታ ተጠናቆ ሥራ ለመጀመር የምርቃት ሥነ-ስርዓቱን እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ተዘግቦአል።

https://p.dw.com/p/2T7rb
Karte Zentral Afrika
ምስል DW

Ethio- Kenya Highway* - MP3-Stereo

መንገዱ ኬንያ እንብርት ላይ ከምትገኘዉ ከእስኦሎ ከተማ ተነስቶ፤ ወደ ሜሪሌ ከተማ፣ ከሜሪሌ ማርሳቢት፣ ከማርሳቢት ቱሪቢ፤ በመጨረሻም ከቱርብ ሞያሌ ድረስ እንደተዘረጋ ዘገባዉ ያሳያል። ኢትዮጵያንና ኬኒያን በኢኮኖሚ ለማተሳሰር በጣም ወሳኝ መንገድ ነዉ የምሉት በሴሜን ኬንያ የማርሳቡት ከተማ አስተዳዳር የሆኑት አምባሳዳር ኡኩር ያታን ለከተማቸዉ ከፍተኛ የንግድ ለዉጥ ሊያመጣ እንደምችልም ለዶይቼ ቬሌ ገልፀዋል።

መንገዱ ለተጓዦች ክፍት መሆኑን ጠቅሶ፣ በይፋ የሚመረቀዉ በቅርብ መሆኑን ይናገራሉ፣ «የአዉራ ጎዳናዉ የመጨረሻ ኪሎሜትር ባለፈዉ ሳምንት ተጠናቀዋል፣ እናም ጎዳናዉ ከናይሮቢ ተነስቶ እስከ አዲስ አበባ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተገናኝተዋል። ለይፋዊ ምርቃት ትክክለኛ ቀኑ መቼ እንደሆነ በርግጥ አሁን ባይታወቅም፤ በአንድ ወር ግዜ ዉስጥ የሁለቱም አገር መሪዎች በይፋ እንደሚከፍቱት ይጠበቃል።»

 

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ