የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ለዉጥ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 5 2010ማስታወቂያ
ዶቼቬለ ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሀን መድረክ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን እየተካሄደ ነው። የዘንድሮው ስብሰባ መበላለጥ ወይም ልዩነቶች በሚታዩባት ዓለማችን የመገናኛ ብዙሀን አዘጋገብ እና ሚና ላይ ያተኮረ ነው። በሥስት ቀናቱ ስብሰባ ከ120 ሐገራት እንደመጡ የሚገመቱ ከ2ሺህ በላይ ሰዎች ተካፍለዋል። በዘንድሮው መድረክ ላይ ከተካፈሉት ኢትዮጵያውያውያን መካከል ሁለቱ ዛሬ ወደ ስቱድዮአችን ብቅ ብለው ነበር። እነርሱም የድረ ገጽ አምደኛው በፍቃዱ ኃይሉ እና የራድዮ ጋዜጠኛ ሲሳይ ውብሸት ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚደረገው ፈጣን ለውጥ እና ስለ መገናኛ ብዙሀን ይዞታ ኂሩት መለሰ አነጋግራቸዋለች።
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ