1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሕጋዊነት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 1 2009

የዉጪ መንግሥታት፤ የመብት ተሟጋቾች እና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት መንግሥት አዋጁን እንዲያነሳ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም እስካሁን ሰሚ አላገኙም

https://p.dw.com/p/2ch3X
Äthiopien Notstände in Amhara
ምስል DW/J. Jeffrey

mmt (Beri.Toronto) Äthiopien Notstand-Analyse - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቀስቅሶበት የነበረዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞና አመፅ ለመገደብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ 7 ወር አለፈዉ።የዉጪ መንግሥታት፤ የመብት ተሟጋቾች እና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት መንግሥት አዋጁን እንዲያነሳ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም እስካሁን ሰሚ አላገኙም።ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች ደንቡ የዜጎችን የመንቀሳቀስ መብት የሚጋፋ ነዉ ባዮች ናቸዉ።የሕግ ባለሙያዎች በበኩላቸዉ አዋጁ ዓለም አቀፍ ሕግጋትንና የአፍሪቃን መተዳደሪያ ደንብ የሚቃረን ነዉ በማለት መንግሥትን ይወቅሳሉ።የቶሮንቶዉ ወኪላችን አክመል ነጋሽ ባለሙያ አነጋግሯል።

አክመል ነጋሽ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ