1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአመራር ምርጫ መራዘም

ሐሙስ፣ ጥር 3 2010

በመጪው ቅዳሜ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሊካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአመራር ምርጫ ለሁለት ወራት ተራዘመ። ምርጫው የተራዘመው የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማሕበራት ፌዴሬሽን (FIFA) እና የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፈደሬሽን፤ (CAF) በጋራ የምርጫ ሂደቱ የሕግ ጥሰት እንዳለበት ካሳሰቡ በኋላ ነው።

https://p.dw.com/p/2qhwj
Fussball Europameisterschaft der Frauen 2017 Deutschland vs Dänemark
ምስል imago/foto2press/O. Zimmermann

በመጪው ቅዳሜ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሊካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአመራር ምርጫ ለሁለት ወራት ተራዘመ። ምርጫው የተራዘመው የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማሕበራት ፌዴሬሽን (FIFA)  እና የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፈደሬሽን፤ (CAF) በጋራ የምርጫ ሂደቱ የሕግ ጥሰት እንዳለበት ካሳሰቡ በኋላ ነው። የሕግ ጥሰት ከተባሉት መካከል፣ ተጠባባቂ አስመራጭ ኮሚቴ አለመመረጡ እና አስመራጭ ኮሚቴን ደግሞ መምረጥን ይመለከታል። ለዝርዝሩ ዘገባ አዲስ አበባ የሚገኘው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚያብሄር።


ዮሐንስ ገብረ እግዚያብሄር
ልደት አበበ