የኢትዮጵያ እና የግብፅ ግንኙነት
ሐሙስ፣ ጥር 10 2010ማስታወቂያ
ትናንት ካይሮ የገባዉ የኢትዮጵያ መንግሥት የልዑካን ቡድን የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታ አልሲሲ ከመሩት ከግብፅ አቻዎቹ ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርሟል።የሁለቱ መንግሥታት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ካይሮ ዉስጥ የተሰበሰቡት ኢትዮጵያ በምታስገነባዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሰበብ የሁለቱ ሐገራት ግንኙነት መሻከሩ በሚነገርበት ወቅት ነዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም እንዳሉት ግን ያሁኑ ጉብኝትና ስምምነት የሁለቱ ሐገራት ግንኙነት ከአባይ ያለፈ ግንኙነት እንዳላቸዉ የሚያረጋግጥ ነዉ።አቶ መለስን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግራቸዋል።
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ