የኢትዮጵያ አትሌቶች ቅሌት
ረቡዕ፣ የካቲት 30 2008ጉዳዩ አገሪቷ በአትሌትክስ ያላትን እዉቅና እና ለዘመናት የገነባችዉን ክብር በከባድ ሊጎዳ እንደሚችል የሚናገሩ አሉ። የስፖርት ጋዜጠኛ ምስጋናዉ ታደሰ አንዱ ነዉ።
ባለፈዉ አርብ የካትት 25, 2008 ዓ/ም የእትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን በጠራዉ ስብሰባ ወደ ከ300 በላይ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን እንዴ ፌዴሬሸኑ አሁንም እንደ አስፈላጊነቱ የሚጠረጠሩ አትሌቶችን የምርመራ ናሙና እንደሚወስድ ዘገባዎች ያሳያሉ። በዓለም አቀፉ የፀረ ጉልበት ሰጭ መድሐኒት ተቋም «WADA» በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ ደንብ አንቀፅ 38 መሰረት ሦስቱ የተወገዱት አትሌቶች በሚቀጥሉት ሁሉት ወራቶች ዉስጥ ይግባኝ ማለት እንደሚችሉ ጋዜጤኛ ምስጋናዉ ይናገራል።
አትሌቶቹ ይሕን የጉልበት ሰጭ መድሐኒት አወሳሰዳቸዉን በተመለከተ አስልጣኞቻቸዉን ጨምሮ ድካም ይቀንሳል፣ የምግብ ፍላጎት ይከፍታል፤ ጭንቀትን ያስወግዳል በሚል ምክንያት እንደሆነ በስብሰባዉ ላይ የተካፈሉት በፌዴሬሽኑ በህክምና ሙያ የምያገለግሉት ዶክተር አያሌዉ ጥላሁን መግለፃቸዉን ጋዜጠኛዉ ይናገራል።
ጉዳዩን በተመለከተ በዶቼ ቬሌ ደህረ ገፅ ላይ በተደረገዉ ዉይይት ሁኔታዉ እንዳሳሰባቸዉ የተለያዩ አድማጮች አስርድታዋል። ሊያሳድር የምችለዉ ተፅኖም ቀላል እንዳልሆነ እና አትሌቶቹ የራሳቸዉን ጥቅም እንጅ የአገርን ጥቅም እንዳላስቀደሙ ተሳታፊዎቹ ገልፀዋል።
መርጋ ዮናስ
ነጋሽ መሐመድ