የሂዩመን ራይትስ ዋች አስተያየት
ረቡዕ፣ ጥቅምት 2 2009ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት የደነገገችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በጣም እንደሚያሳስበው ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ ።የድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ሃላፊ ሚስ ሌስሊ ሌፍኮ በሰጡት አስተያየት አዋጁ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን ሊገድብ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል ። የኢሬቻን በዓል ለማክበር በሄዱበት በቢሾፍቱ የሞቱት ሰዎች ጉዳይ በዓለም ዓቀፍ ገለልተኛ ወገን እንዲጣራም ሃላፊዋ ጠይቀዋል ። ለኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር መፍትሄ ካሏቸው መካከል በህገ ወጥ መንገድ በፀረ ሽብር ህግ የታሰሩትን ተቃዋሚዎች መፍታት እና ለሞቱት እና ለቆሰሉት ካሳ መስጠት ይገኝበታል ። ያነጋገራቸው የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ