1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ አፋሮች ፓርቲ አቋም

ረቡዕ፣ ሰኔ 13 2010

ድርጅቱ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ዓሊ መሐመድ ዑመር እንደሚሉት ሠላም ለማስፈን የሚደረግ ጥረትን ድርጅታቸዉ ምንጊዜም ይደግፋል።

https://p.dw.com/p/2zxDW
Äthiopien Wissenschaftlerin Forscherin Lulit Tilahun Wolde Afar Triangle
ምስል L. T. Wolde

(Q&A) Eritrean Afar Reax on Eritrea - MP3-Stereo

የኤርትራ አፋሮች የስደት መንግሥት የተባለዉ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት ሥር የሰደደዉን የሁለቱን ሐገራት ጠብ እና ግጭት ለማስወገድ የጀመሩትን ጥረት እንደሚደግፍ አስታዉቋል።የድርጅቱ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ዓሊ መሐመድ ዑመር እንደሚሉት ሠላም ለማስፈን የሚደረግ ጥረትን ድርጅታቸዉ ምንጊዜም ይደግፋል።ይሁንና የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት ሠላም ለማዉረድ የሚያደርጉት ጥረትም ሆነ ድርድር የአፋርን ሕዝብ ፍላጎት እና ጥቅም ካላካተተ ባካባቢዉ ዘላቂ ሠላም ማስፈን አይቻልም።

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ