አደገኛው አማጺ ቡድን በኡጋንዳ
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 28 2008ማስታወቂያ
የኡጋንዳ ጦር አደገኛውን የዓማጺ ቡድን ማደን ሊያቆም መሆኑን በሀገሪቱ የጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል ካቱንባ ዋማላ በኩል አስታውቋል። ጦሩ ራሱን «የጌታ ተከላካይ ጦር» በእንግሊዝኛ ምኅጻሩ LRA እያለ የሚጠራው የአማጺ ቡድንን ማደኑን ትቶ ሊወጣ መሆኑ የገለጠው የሚተባበረው በማጣቱ ነው። የአፍሪቃ ኅብረት ጦር በቦታው ቢገኝም ከጫማ አንስቶ አጠቃላይ ወጪያችንን ራሳችን ማውጣታችን ኢኮኖሚያችንን አናግቶታል ሲሉ የጦር ሠራዊቱ ቃል አቀባይ ሻለቃ ፓዲ አንኩንዳ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ